View in English alphabet 
 | Monday, September 06, 2010 ..:: ቅዱሳን መላእክት ::.. Register  Login
if ye have word of exhortation for the people, say on

መስገድ የሚለው ቃል መዋረድ፣ ማጐንበስ፣ መንበርከክ፣ መደፋት፣ በግንባር መውደቅ፣ ግንባርን ምድር አስነክቶ መሬት ስሞ መመለስ ነው በማለት የአለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ መዝገበ ቃላት ያትታል፡፡ በቤተ ክርስቲያናችን ስግደት የአምልኮና የጸጋ ተብሎ ይከፈላል፡፡ የአምልኮ ስግደት ለእግዚአብሔር ብቻ የሚቀርብ ሲሆን የጸጋ ስግደት ደግሞ እግዚአብሔር ላከበራቸው ቅዱሳን ሰዎችና መላእክት የሚቀርብ ነው፡፡

  ተጨማሪ ያንብቡ



ቅዱሳን መላእክት በእግዚአብሔርና በሰው መካከል ለአገልግሎት የሚፋጠኑ ናቸው፡፡ ከእግዚአብሔር ዘንድ ምሕረትንና ቸርነትን ወደ ሰው ልጆች፣ የሰዎችንም ጸሎትና ልመና ወደ እግዚአብሔር የሚያደርሱ ናቸው፡፡
ቅዱሳን መላእክት በመንገዳችን ሁሉ እንደሚጠብቁን ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት ሲያስረዳ እንዲህ ብሏል #በመንገድ ሁሉ ይጠብቁህ ዘንድ መላእክቱን ስለ አንነተ ያዝዛቸዋልና፣ እግርህም በድንጋይ እንዳትሰናከል በእጆቻቸው ያነሡሃል$ (መዝ. 90/91/-11)፡፡
  ተጨማሪ ያንብቡ



የመላእክት መላእክት በአፈጣጠራቸው ረቂቃን መናፍስት በመሆናቸው እንደ ሥጋ ለባሽ ፍጥረታት አይበሉም፣ አይጠጡም፣ አያገቡም (ማቴ 22$30፡፡ ሉቃ 24$39)፡፡ ጾታም የላቸውም፡፡ አንዳንድ ሰዎች ግን መላእክት በአንድ ወቅት ከሰው ልጆች ጋር እንደወደቁ አድርገው ይናገራሉ፡፡ ለዚህም መረጃ አድርገው ለማቅረብ የሚሞክሩት ‹‹የእግዚአብሔር ልጆች የሰውን ሴቶች ልጆች አገቡ›› የሚለውን ኃይለ ቃል ነው (ዘፍ.6$2)፡፡
  ተጨማሪ ያንብቡ



(ከብርሃኑ ጎበና)
ቅዱስ ማለት የተለየ፣ የተከበረ፣ የተመሰገነ፣ የተመረጠ ማለት ነው፡፡ ቅዱሳን መላእክት ስንልም የተመሰገኑ፣ ከርኵሳን መላእክት የተለዩ፣ ክቡራን መላእክት ማለታችን ነው፡፡ መላእክት ሁለት ወገን ናቸው፡፡ ብርሃናውያን መላእክትና የጨለማ አበጋዝ የሆነው የዲያብሎስ ሠራዊት የሆኑት እኩያን መላእክት፡፡ ስለዚህ የእግዚአብሔርን መላእክት ከሌሎቹ መላእክት በአጠራር የምንለያቸው ቅዱስ በሚል ቅጽል ነው፡፡
  ተጨማሪ ያንብቡ



 የቅዱስ ሚካኤል ስሞች
መላእክት ቁጥራቸው እጅግ ብዙ ቢሆንም በ99 ነገድ የተከፈሉና አለቆችም ያሏቸው ናቸው፡፡ የእነዚህ ሁሉ መላእክት አለቃ የሆነው ቅዱስ ሚካኤል ነው፡፡ በትህትናው ልዕልናን ያገኘው ቅዱስ ሚካኤል በእግዚአብሔር ዘንድ የተሰጠው ክብር ከማንኛውም መልአክ የበለጠ መሆኑን መጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ አስቀምጦታል፡፡

  ተጨማሪ ያንብቡ



Copyright 2007 by Mahibere Kidusan USA Center  | Terms Of Use | Privacy Statement