|
የጌታችን ትንሳኤ በአበው ዘንድ በምሳሌ የተመሰለ፣ በነቢያት በትንቢትና በምልክት የተነገረ፣ በተስፋ የተጠበቀ የድኅነታችን ታላቅ በር ነው፡፡ የጌታችንን የወንጌል ምሥራች የሰበኩ ሐዋርያትም የጌታን ትንሳኤ በደስታና በጽናት መስበካቸው ትንሳኤው በኃጢአትና በሞት ላይ የተደረገ ታላቅ ድልና የድኅነት የምሥራች በመሆኑ ነው፡፡ ስለዚህም የትንሳኤው ምስክሮች ሆነዋል፡፡ /የሐ.ሥራ 2፡32/ ጌታ የተነሳበት ሰንበተ ክርስቲያንም የበዓላት በኩር፣ የዘላለም ሕይወት ቀብድ፣ ዘላለማዊት መባሏ የጌታ ትንሳኤ የምዕመናን የዘላለም ሕይወት ትንሳኤ በኩር በመሆኑ ነው፡፡ /1ኛቆሮ. 15፡20/
ተጨማሪ ያንብቡ
|
|
(ዲ/ን ዮሐንስ ልሳነወርቅ)
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ማታ ማታ እየወጣ የሚያድርባት፣ሐሙስ ሌሊት በይሁዳ በኩል ለአይሁድ ተላልፎ የተሰጠባት፣ሐዋርያት ስለ ነገረ ምጽአት ጠይቀው የተረዱባት፣ከሙታን ተለይቶ በተነሣ በአርባኛው ቀን ጌታችን ያረገባት ተራራ -ደብረ ዘይት። ዐርገ የሚለው የግዕዝ ግስ ዐረገ፣ወጣ በሚሉት የአማርኛ ቃላት የሚፈታ ሲሆን ዕርገት የሚለው ስምም ማረግን፣ መውጣትን፣አወጣጥን ያመለክታል።(አ.ኪ.ክ መ.ቃ)
አስቀድሞ ክቡር ዳዊት እንደተናገረው መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደቀመዛሙርቱ እያዩት ወደ ሰማይ ዐርጓል። ዐርገ እግዚአብሔር በይባቤ፤ወእግዚእነ በቃለ ቀርን - እንዲል መዝ. 46፥5። ጌታችን በእውነት እንዳረገ ይኽም ሊታመን የማይችል እንዳልሆነ የቤተ ክርስቲያን ሊቅ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ያስረዳል። ሕማም የሚስማማው ግዙፍ ሥጋን ተዋሕዶ ሳለ ከስቅለቱ አስቀድሞ በባሕር ላይ ከሄደ፡ ዛሬ ነፋስን ከፍሎ ሲያርግ ቢታይ ማንም ማን አይጠራጠር፤ሥጋው አልተለወጠምና። ሃይ.አበው ዘዮሐ.አፈ.ክፍል 13 ቁጥር 15
ተጨማሪ ያንብቡ
|
|
(በቀሲስ ስንታየሁ አባተ)
በኢሳይያስ ዘመን የነበሩ እስራኤላውያን የተናገሩት ቃል ነው:: እስራኤላውያን የሚጾሟቸው ብዙ አጽዋማት ነበሯቸው:: ለምሳሌ ያህልም ብናይ በሳምንት ሁለት ጊዜ በሳምንት ሁለት ቀን ይጾሙ እንደነበር በሉቃስ ወንጌል ምዕ. 18¸12 ላይ ያለው ቃል ያስረዳል:: ማክሰኞና ሐሙስ ሊቀ ነቢያት ሙሴ ወደ ደብረ ሲና የወጣበትንና ከዚያ የወረደበትን ዕለት ለማሰብ እስራኤላውያን በሳምንት ሁለት ቀኖች ይጾሙ ነበR:: በነቢዩ በዘካርያስ ትንቢትም ላይ እግዚአብሔር እስራኤላውያንን እንዲህ ብሎ አዝዟቸዋል::"የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔር ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል የአራተኛው ወር ጾም የአምስተኛውም የሰባተኛውም የአስረኛውም ወር ጾም ለይሁዳ ቤት ደስታና ተድላ የሀሴትም በዓላት ይሆናል ስለዚህም እውነትንና ሰላምን ወደዱ" ተብሎ ለእስራኤላውያን ከእግዚአብሔር ዘንድ በነቢዩ በኩል በተነገራቸው መሠረት የተጠቀሱትን ይጾሙ ነበረ:: ዘካ. 8 18ና19
ተጨማሪ ያንብቡ
|
|
ሕዝ 34፡7
መምህር ዕርገተ ቃል ይልማ
ከዐበይት ነቢያት አንዱ የሆነው ሕዝቅኤል ከጌታ ልደት 597 ዓመት በፊት የተነሳ ነቢይ ነው፡፡ይህ ታላቅ ነቢይ የእሥራኤል ልጆች ወደ ባቢሎን ተማርከው በስደት በሄዱ ጊዜ
ከምርኮኞች አንዱ በመሆን እስራኤላውያን የደረሰባቸውን መከራና ስቃይ በዐይኑ ለማየት ጩኸታቸውንም በጆሮው ለመስማት ችሏል፡፡ ኢየሩሳሌም ለከፋ ውድቀት ከመዳረጓ በፊት ሕዝቡ ራሳቸውን በንስሐ ወደ እግዚአብሔር እነዲያቀርቡ መክሯል፡፡ይሁን እንጂ ከበደላቸውና ከኃጢአታቸው ተመልሰው በጽድቅ መንገድ ሊጓዙ ስላልቻሉ የተለያየ መከራ ደረሶባቸዋል፡፡
ተጨማሪ ያንብቡ
|
|
እግዚአብሔርን የሚወዱ መንፈሳውያን ሰዎች ሁሉ በዚህ የትንሣኤ በዓል ደስ ይበላቸው፡፡ ጠቢባን (የእግዚአብሔር) አገልጋዮች ወደ ጌታቸው ደስታ ይግቡ፡፡ የጾምን ቀንበር ተሸክመው የነበሩ ዛሬ ዋጋቸውን ይቀበሉ፡፡
ተጨማሪ ያንብቡ
|
|
|