View in English alphabet 
 | Monday, September 06, 2010 ..:: ንቁ ::.. Register  Login
if ye have word of exhortation for the people, say on

(አዲስ አበባ)፡- ዕለተ ዓርብ መስከረም 30/2001 ዓ.ም ነው፡፡ ሰዓቱም ከጠዋቱ 2 ሰዓት፡፡ እንደተለመደው ሃይማኖታዊ ተግባር ሁሉ በመናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ (አራዳ ጊዮርጊስ) ቤተ ክርስቲያን ኪዳን ከተደረሰ በኋላ ምእመናን ወደየቤታቸው ሊሄዱ ሲዘጋጁ ነበር፤ ከቤተመቅደሱ አቅራቢያ ያልተለመደ አስደንጋጭ ድምፅ የተሰማው፡፡


ከነጫማው ወደ ቤተ ክርስቲያን የገባ አንድ ግለሰብ ወለል ላይ ነጠላ አንጥፎ የሙስሊም የእምነት ሥርዓት በሚመስል መልኩ እየሰገደ «አላህ ወአክባር፣ አላህወአክባር፣ ሥዕል ይውረድ፣ መስኪድ ይሠራ .. አላህወአክባር» እያለ ይጮሃል፡፡ ባልተለመደው ክስተት የተደናገጡት ምእመናን ዝም አላሉም ግለሰቡን ይዘው የደብሩን ጥበቃ ሠራተኛ ጠርተው ከቤተ መቅደስ እንዲወጣ አደረጉት፡፡

  ተጨማሪ ያንብቡ



ሀ. ቅድስናው፡- እስላሞች ብሉይ ኪዳንንና ሐዲስ ኪዳንን እናከብራለን የሚሉ ቢሆንም ለቁርአን ግን ልዩና ከሁሉም ነገር በላይ የሆነ ቦታ ይሰጣሉ፡፡ የመጻሕፍት ሁሉ እናት ይሉታል (43¸3)፡፡ ይዘቱን መመርመር ድፍረትና ኃጢአት ነው፡፡ በጥንቃቄና በንጽሕና እንጂ እንዲሁ እንደተገኘም አይነካም፡፡
  ተጨማሪ ያንብቡ



የቁርዓን እያንዳንዱ ክፍል "አያ" ይባላል፡፡ ይህም በዐረብኛ ተአምር ማለት ነው፡፡ መሐመድ ቁርአን የእሱ ብቸኛ ተአምር መሆኑን ይናገራል፡፡ ሆኖም ቁርአን በእርሱ የሕይወት ዘመን በመጽሐፍ መልከ አልነበረም፡፡ በቁርአን የይዘት ቅደም ተከተል ላይ ያለው ልዩነት ዋናው ምክንያት የመጨረሻውን የቁርአን ስብስብ ይዘትና ቅደም ተከተል ለማጽደቅ ወይም ይሁንታ ለመስጠት መሐመድ በሕይወት ያልነበረ መሆኑ ነው፡፡

  ተጨማሪ ያንብቡ



እንደ እስልምና ትውፊት የሱራዎቹን (መጻሕፍቱን) መገለጥ መሐመድ የተቀበለው በጂብሪል መልአክ በሦስት ጊዜያት ውስጥ ነው፡፡ የመጀመሪያው የመካ ጊዜ ሲባል ከ 611-615 ድረስ ያለው ነው፡፡ በዚህ ጊዜ ያሉት ሱራዎች በቁርአን ያሉት ብዙዎቹ ማስጠንቀቂያዎችና አላህን በተመለከተ ድምዳሜያቸውን አመላካች በመሆኑ ሰፊ ገለጻዎች ያሉበት ነው፡፡ ሁለተኛው ጊዜ ደግሞ ሁለተኛው የመካ ጊዜ ተብሎ የሚታወቅ ሲሆን (615-622) ብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ ምንጮችን የሚመስሉ ዶግማ ነክ ጉዳዮች ያሉበት ነው፡፡ እስልምና ብቻውን ትክክለኛ ሃይማኖት ነኝ ማለት የጀመረው በዚህ ጊዜ ነው፡፡ ሦስተኛው ጊዜ የመዲና ጊዜ የሚባለው ሲሆን፤ (623-632) መዲናን የማከለና እስከ መሐመድ ሞት ያለው ጊዜ ነው፡፡
  ተጨማሪ ያንብቡ



1. አላህ የእግዚአብሔር ስም ነውን?
በእስልምና ሃይማኖት የአምላካቸው ስም አላህ ነው፡፡ ይህ ስም ምንጩ ከየት ነው? በእርግጥስ እነርሱ (እስላሞች) እንደሚሉት ይህ ስም በፊት በብሉይ ኪዳን ኋላም በሐዲስ ኪዳን የተገለጸው አምላክ ስም ነው? ክርስቲያኖችና እስላሞችስ አምላካቸው አንድ ነው? ልዩነት ካለስ የስም ልዩነት ብቻ ነው ወይስ መሠረታዊ የሆነ የ‹ምን›ነትና የ‹ማን›ነት ልዩነት አለ?
  ተጨማሪ ያንብቡ


Page 1 of 3First   Previous   [1]  2  3  Next   Last   

Copyright 2007 by Mahibere Kidusan USA Center  | Terms Of Use | Privacy Statement