View in English alphabet 
 | Monday, September 06, 2010 ..:: መዝሙራት ወቅዳሴያት ::.. Register  Login
if ye have word of exhortation for the people, say on

ሀ. መዝሙር እግዚአብሔርን በተመስጦ ለማመስገን ለመቀደስ
ለ. መዝሙር ወደ እግዚአብሔር ልባዊ ጸሎት ወይም ልመናን በማራራት ለማቅረብ

ሐ. መዝሙር ለመማሪያና ለማስተማሪያ ወይም ልብን ለማነፅና ነፍስን ለማስደሰት (መንፈስን ለማደስ)፣ ለምክር፣ ለተግሣጽና ደግሞም ለመጽናትና ለማጽናናት እጅግ አድርጎ ይጠቅማል፡፡ መዝሙር ወይም ዜማ የተጀመረው በአራቱ ሰማያት ማለት በሰማያዊት ኢየሩሳሌም በኢዮር፣ በራማና በኤረር ያሉ መላእክት እግዚአብሔር ፈጣሪያቸውን ያለ ዕረፍት ሲያመሰግኑት ነው፡፡ ይህንንም ሲያረጋግጥ ነቢዩ ኢሳይያስ ‹‹እግዚአብሔርን በረጅምና ከፍ ባለ ዙፋን ላይ ተቀምጦ አየሁት፡፡››

  ተጨማሪ ያንብቡ



(ዐቢይ ኃ/ጊዮርጊስ)
 ለማናቸውም ነገር መነሻና መግቢያ ሊኖረው ያስፈልጋል፡፡ ስለሆነም በርእሰ ነገራችን ባሕረ አድማስ ክልል የብዙ ቃላት መሣፈሪያ የሆነ መርከብ አነጋገር ከመመለሻችን አስቀድሞ ለዚህ ጥልቅና ስፉሕ ለሆነው ርእሳችን መርሕ (ትርጓሜ) ልንሰጠው የተገባ ነው፡፡ እንዲህም ከሆነ መዝሙር ምንድን ነው; የሚለውን መጠይቅ ለርእሰ ነገራችን ሐተታዊ ፍሬ ነገር መነሻ በማድረግ መሠረታዊ ትምህርታችንን እንጀምራለን፡፡
  ተጨማሪ ያንብቡ



ጥንታውያን ኦሪየንታል ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት በመባል የሚጠሩት ኢትዮጵያ፣ ግብፅ፣ ሶርያ፣ አርመንና ሕንድ በእምነታቸው (የተዋሕዶን ትምህርተ ሃይማኖት በመጠበቃቸው) አንድ ቢሆኑም በሥርዓተ መዝሙር (ማለትም በመዝሙር ዜማና አቀራረብ) ግን በመጠኑ ይለያያሉ፡፡ ለምሳሴ ግብፃውያን የዜማ መሣሪያዎቻቸው ሁለት ብቻ ናቸው፡፡ ነገር ግን ከቅዳሴ በፊትና በኋላ በመዘመራችን፣ ሌሊት ማኀሌት በመቆማችን፤ ሥርዓታችን ተመሳሳይ ነው፡፡ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን መዝሙራትን #ኣርቶዶክሳዊ$ ነው የምትለው ትምህርተ ሃይማኖትዋን፣ ሥርዓትዋን፣ ታሪኳንና ትውፊትዋን ሲጠብቅ ብቻ ነው፡፡ ለምሳሌ በግብፃውያን ሥርዓት ከዜማቸውና ከመዝሙር መሣሪያዎቻቸው ውጭ መዘመር አይፈቀድም፡፡
  ተጨማሪ ያንብቡ



Copyright 2007 by Mahibere Kidusan USA Center  | Terms Of Use | Privacy Statement