|
ከመልአከ ሰላም ደጀኔ ሺፈራው
«አልብኪ ነውር ወኢምንትኒ ላዕሌኪ፤» መኃ 4:7
የትንቢተ ነቢያት ማረፊያ ፡-የስብከተ ሐዋርያት መነሻ.የሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ምሥጢር ነገረ ማርያም ነው፡፡ ያለ ነገረ ማርያም ነገረ ክርስቶስን መናገር አይቻልም፡፡ በክርስትና ሃይማኖት ታሪክ የተነሡ አያሌ መናፍቃን የመጀመሪያ ችግራቸው የነገረ ማርያምን አማናዊ ትምህርት መቀበል ነበር ፡፡ ያም ችግራቸው ክርስቶስን በትክክል እንዳያምኑት አድርጓቸዋል፡፡ በነገረ ማርያም ላይ የተጣራ ትምህርትና እምነት ቢኖራቸው ኖሮ ለኑፋቄ አይጋለጡም ነበር ፡፡ ንስጥሮስ፡- «አምላክ ወልደ አምላክ» ብሎ በክርስቶስ ለማመን የተሳነው « ወላዲተ አምላክ . ወላዲተ ቃል. እመ እግዚአብሔር » ብሎ በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም ለማመን በመቸገሩ ነበር፡፡ PDF
ተጨማሪ ያንብቡ
|
|
ኪዳን የሚለው ቃል ተካየደ ከሚለው የግእዝ ግስ የወጣ ሲሆን ትርጉሙም ተማማለ፣ ተስማማ፣ ውል ገባ ማለት ነው፡፡ ኪዳነ ምሕረት ማለትም ደግሞ የምሕረት ቃል ኪዳን ማለት ነው፡፡ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለእመቤታችን ድንግል ማርያም ስለሰው ልጆች ይቅርታ የገባላት ቃል ኪዳን ነው፡፡ እግዚአብሔርን ለሚፈሩት፣ ለሚያከብሩት፣ ለሚወዱትና ለሚወዳቸው ሁሉ በተለያዩ ጊዜያት ብዙ ኪዳናትን ሰጥቷል፡፡ በቅዱሳት መጻሕፍት ከሚጠቀሱት ውስጥ ለአብነት ያህል የሚከተሉትን እንመልከት፡፡
ተጨማሪ ያንብቡ
|
|
|
|
ቤተ ክርስቲያናችን ለምን ስለ እመቤታችን ዘወትር እንደምታስተምር አንዳንድ ሰዎች ግር ሲላቸው ይታያል፡፡ እንዲያውም ‹‹አላዋቂ ሳሚ...›› እንዲሉ ስለ እመቤታችን ማስተማå ስለ ጌታችን እንዳታስተምር አድርጓታል ብለው የሚናገሩም አሉ፡፡ ቤተ ክርስቲያናችን ግን ስለ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የምታስተምረው ለርሷ ካላት ልዩ ፍቅር ብቻ ወይም ስለጌታችን የምታስተምረው ለርሷ ካላት ልዩ ፍቅር ብቻ ወይም ስለጌታችን የምታስተምረው አልቆባት አይደለም፡፡ ምክንያቱም ከኢትዮጵያ ሊቃውንት በላይ ለነገረ መለኰት ምሁርና ጥንቁቅ ከማግኘት የሰማይን ስፋት ልክ ማግኘቱ ሳይቀል አይቀርም፡፡
ተጨማሪ ያንብቡ
|
|
እንኳን ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም የልደት በዓል አደረሳችሁ፡፡
የዛሬ 2015 ዓመታት ወደ ኋላ ዘወር ብለን ስንመለከት ታሪክን የሚለውጥ አንድ ድንቅ ክስተት መፈፀሙን እናገኛለን፡፡ ይህም የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ልደት ነው፡፡ ልበ አምላክ የተባለ ነቢየ እግዚአብሔር ዳዊት መሠረቶቿ የተቀደሱ ተራሮች ናቸው ያላትም እርሷን ነው (መዝ. 88፡1)፡፡
ተጨማሪ ያንብቡ
|
|
|