|
የእግዚአብሔርን ስም በከንቱ መጥራት ሲባል ምን ማለት ነው? የአምላካችን የእግዚአብሔር ስም የከበረ በመሆኑ እንደተገኘ የሚጠሩት፣ እንደአጋጠመ የሚናገሩት አይደለም፡፡ ይልቁንም በመፍራትና በመንቀጥቀጥ በትሕትና ሆነው ሊጠሩት የሚገባ ክቡር ስም ነው፡፡ ይሁን እንጂ አንዳንድ ሰዎች የእግዚአብሔርን ስም ያለአግባብ በነገራቸው ሁሉ ውስጥ ሲያስገቡት፣ ሥፍራም ጊዜም ሳይመርጡ እንደፈለጉት ሲጠሩት ይስተዋላሉ፡፡ እንደዚህ ዓይነት ሰዎች እምነትና ፊሪሃ እግዚአብሔር አላቸው ለማለት አያስደፍርም፤ ምክንያቱም የሚያምኑና
ተጨማሪ ያንብቡ
|
|
መሪዎችን ወይም ታላላቆችን ማምለክ
መጽሐፍ ቅዱስ ‹‹ለዋኖቻችሁ ታዘዙና ተገዙ፡፡ እነርሱ ስለነፍሳችሁ ይተጋሉ›› ይላል (ዕብ.13÷17)፡፡ ይህ የሐዋርያው አባባል ‹‹ታዘዙአቸው አታምጹባቸው›› እንጂ ‹‹በእግዚአብሔር ፈንታ አምልኳቸው›› የሚል አይደለም፡፡ መሪዎችንም ሆነ መንፈሳዊ አባቶችን ለመሪነታቸውና ለአባትነታቸው በሚገባው መጠንና ወሰን በመታዘዝ ልንገዛላቸው ከሚገባ በቀር ከእግዚአብሔር ጋር አወዳድረን ልናመልካቸውና ከፈጣሪአችን የሚያጣላን ትእዛዝ በሚያዝዙን ጊዜም እሺ በጀ ብለን ልንቀበላቸው አይገባም፡፡
ተጨማሪ ያንብቡ
|
|
ዝናን ማምለክ
አንዳንድ ሰዎች በሚገባ ወይም በማይገባ ነገር ለዝናቸው ወይም ለሚያውቁት ሰው ዝና ሲሟገቱ ይታያሉ፡፡ የራሳቸውን ወይም የሚሟገቱለትን ሰው ስህተት በመሸፈን፣ ጥፋቱን በመከለል አንዱን ሰው ከቤተ ክርስቲያን፣ ከሕዝብ ወይም ከመንግሥት በላይ አድርገው ዝናውን ለመጠበቅ ይጥራሉ፡፡ መሳሳታቸውን ወይም የሚሟገቱለት ሰው ስህተት መፈጸሙን ቢያውቁም ስለሚያገኙት ምድራዊ ዝና ሲሉ እውነትን ይደብቋታል፡፡ ይህ ደግሞ ለዝና መገዛትና ዝናን ማምለክ ነው፡፡ ጸሐፊው ስለዝና የሚሟገቱትን አስመልክቶ ‹‹የባልንጀራ ዓይን ለስህተት የተደፈነች ናት፡፡ የጠላት ዓይን ግን እያንዳንዱን ጥፋት ትገልጣለች›› ብሎአል፡፡ የዚህ ዓይነቱ ባልንጀራ ጠቃሚ አይደለም፡፡ ጥፋቴን ዓይቶ ካልነገረኝ እንድስተካከልም ካልመከረኝ ለባዶነቴ ቢሟገትልኝ በመጨረሻ ከውድቀቴ ሊያነሣኝ አይችልምና አይረባኝም፡፡ ‹‹እውነተኛ ባልንጀራ መስተዋት ነው›› ይባል የለ፡፡
ተጨማሪ ያንብቡ
|
|
(ቀሲስ እሸቱ ታደሰ)
ሰዎች ይህን ትእዛዝ በሚያነቡበት ወይም በሚሰሙበት ጊዜ ‹‹ይህ ከእኔ ጋር ምን ግንኙነት አለው፣ ይህ ሊነገር የሚገባው ለከሐድያንና ለመናፍቃን ወይም ከሥጋዊ ዕውቀታቸው የተነሣ አሊያም ከፍልስፍና በመነጨ ሁኔታ ከሃይማኖት ያፈነገጡትን ነው፡፡ እኔ ግን በሳምንት ይኽን ያህል ቀን እጾማለሁ፣ አሥራት አወጣለሁ፣ በየሰዓቱ እጸልያለሁ፣ ከልቤ እዘምራለሁ፣ የቤተ ክርስቲያን መርሐ ግብሮችን ያለማቋረጥ እከታተላሁ፣ ስለሆነም ይህ ትእዛዝ አይመለከተኝም›› ይሉ ይሆናል፡፡
ተጨማሪ ያንብቡ
|
|
በለብለብ ክርስቲያንና በኦርቶዶክሳዊ ክርስቲያን መካከል ትልቅ ልዩነት አለ፡፡ ምክንያቱም ኦርቶዶክስ ማለት ርቱዕ በሃይማኖቱ፣ ርቱዕ በምግባሩ ነውና፡፡ ኦርቶዶክስ የሚለው ቃል የግሪክ ሲሆን ኦርቶ ማለት የቀና የተስተካከለ ርቱዕ ማለት ሲሆን፣ ዶክሳ ማለት ደግሞ ሃይማኖት ማለት ነው፡፡ ኦርቶዶክስ ማለትም የቀና የተስተካከለ ማለትም ርቱዕ የሆነ ሃይማኖት ማለት ነው፡፡
ተጨማሪ ያንብቡ
|
|
|