|
አንዳንድ ሰዎች የሕፃናትን ጥምቀት ሲነቅፉና ትክክለኛ ጥምቀትም እንዳልሆነ ሲናገሩ ይሰማሉ፡፡ ተራ ትችት ግን መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት የሌለው ነው፡፡ እነዚህ ክፍሎች ራሳቸው ከአእምሮአቸው አመንጭተው ላስተማሩት ሐሰተኛ ትምህርት መጽሐፍ ቅዱስ ያስተማረው አስመስለው ለማቅረብ ሲሞክሩም ይስተዋላሉ፡፡
ተጨማሪ ያንብቡ
|
|
ኖኀና ቤተሰቡ ከጥፋት የዳኑባት መርከብ የአማናዊቱ ቤተክርስቲያን ምሳሌ መሆንዋ በመጽሐፍ ቅዱስ የተረጋገጠ ነው፡፡ ፈሪሃ እግዚአብሔር በልቡናቸው ያደረው ኖኀና ቤተሰቡ ከጥፋት ሲድኑ እግዚአብሔርን ድምፅ ያልሰሙት የኖኀ ዘመን ለአማናዊው ጥምቀት ምሳሌነት እንዳለው ሊቀ ሐዋርያት ቅዱስ ጴጥሮስ ሲገልጽ (ሲያስተምር) #ጥቂቶች ማለትም ስምንት ነፍስ በውኃ የዳኑበት መርከብ ሲዘጋጅ የእግዚአብሔር ትዕግሥት በኖኀ ዘመን በቆየ ጊዜ ቀድሞ አልታዘዙም፡፡
ተጨማሪ ያንብቡ
|
|
ብርሃኑ ጎበና
መጠመቅ ማለት መነከር፣ መዘፈቅ፣ ውኃ ውስጥ ገብቶ መውጣት ማለት ነው፡፡ ምሥጢረ ጥምቀት የሥላሴ ልጅነት የሚሰጥበት እና የኃጢአት ሥርየት የሚገኝበት ምሥጢር ነው፡፡
ተጨማሪ ያንብቡ
|
|
መሥዋዕተ ኦሪት አልፎ መሥዋዕተ ሐዲስ በመተካት ምሥጢረ ቁርባን የተጀመረው በምሴተ ሐሙስ ነው፡፡[1] ሐሙስ ምሽት በአልዓዛር ቤት ሥርዓተ ቁርባንን መሠረት፡፡ ኢየሱስ እንጀራን አንሥቶ ባረከ፡፡ ቆርሶም ለደቀ መዛሙርቱ ሰጠና ‹‹እንካችሁ ብሉ ይህ ሥጋዬ ነው› አለ፡፡ ጽዋንም አንሥቶ አመስግኖም ሰጣቸው፡፡ እንዲህም አለ ‹ሁላችሁ ከእርሱ ጠጡ ስለ ብዙዎች በኃጢአት ይቅርታ የሚፈስ የአዲስ ኪዳን ደሜ ይህ ነው› አለ፡፡›› (ማቴ.26÷26-29)፡፡
ተጨማሪ ያንብቡ
|
|
የቃሉ ትርጉም
ቁርባን ቃሉ የሱርስትና የዓረብ ሲሆን ትርጉሙም በቁሙ መንፈሳዊ አምኃ፣ መሥዋዕት፣ መባዕ፣ ለአምላክ የሚቀርብ፣ የሚሰጥ ገንዘብ ማለት ነው፡፡ ቃሉን በምልዓት ስንመለከተው ሰው ለአምላኩ የሚያቀርበውን ነገር ሁሉ የሚያካትት ሲሆን በዚህ ርዕሳችን የምንመለከተው ግን ስለ አማናዊው ቁርባን ወይም መሥዋዕት ስለ ምሥጢረ ቁርባን ነው፡፡
ተጨማሪ ያንብቡ
|
|
|