|
ቤተ ክርስቲያናችን ለምን ስለ እመቤታችን ዘወትር እንደምታስተምር አንዳንድ ሰዎች ግር ሲላቸው ይታያል:: እንዲያውም “አላዋቂ ሳሚ …” እንዲሉ ስለ እመቤታችን ማስተመሯ ስለ ጌታችን እንዳታስተምር አድርጓታል ብለው የሚናገሩ አሉ:: ቤተ ክርስቲያናችን ግን ስለ አመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የምታስተምረው ለርሷ ካላት ስለጌታችን የምታስተምረው አልቆባት አይደለም:: ምክንያቱም ከኢትዮጵያ ሊቃውንት በላይ ለነገረ መለኮት ምሑርና ጥንቁቅ ከማግኘት የሰማይን ስፋት ልክ ማግኘቱ ሳይቀል አይቀርም::
ተጨማሪ ያንብቡ
|
|
(በመሐር ቸሬ አበበ)
በፍትሐ ነገሥት መንፈሳዊ አንቀጽ 15 እንደተገለጸው ቅዱሳን አባቶቻችን ሥጋ ለነባቢት ነፍስ እንድትታዘዝና የፈቲው ፆርም እንዲደክም የሚያደርግ የሰውን ልጅ ከእግዚአብሔር ጋር እንዲገናኝ የለመነውም ልመና መልስ እንዲኖረው እጅግም የሰይጣንን ፍላጻ ወይም ጦር ለመስበር የሚያስችል ኃይል ያለው መሣሪያ ጾም ነው፡፡ ነቢየ እግዚአብሔር «በእግዚአብሔር አምላካችን ፊት ራሳችንን ዝቅ እናድርግ፣ በእርሱም ዘንድ ጾምን አወጅኩኝ። ስለዚህ ነገር ጾምን፣ ወደ እግዚአብሔርም ለመንን እርሱም ተለመነን፡፡» እንዳለ የሰው ልጅ የነፍሱን ነገር በማሰብ በጾም እግዚአብሔርን ሊለምን ሊማጸን የሚፈልገውን ሁሉ ሊጠይቅ ይገባል፡፡ ከነቢዩ ዕዝራ የምንማረው በጾም ለሕዝብና ለራስ ለምኖ ዋጋ ማግኘትን ነው፡፡
ተጨማሪ ያንብቡ
|
|
በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ባሕልና ትውፊት መሠረት ይህ የያዝነው የጾም ወራት ከሰባቱ አጽዋማት አንዱና ዋነኛው፣ ጌታ ከተጠመቀ በኋላ የጾመው የአርባ ቀን ጾም ነው፡፡ ምእመናን ጌታቸው ያደረገውን ምሳሌ ተከትለው ይጾሙታል፡፡
ተጨማሪ ያንብቡ
|
|
የጾም ወቅት መንፈሳዊ ተጋድሎዎች የሚበዙበት፣ ለእግዚአብሔር ያለንን ፍቅር የምንገልጥበት፣ እምነታችን የሚጠነክርበት፣ ከዲያብሎስ ጋራ የምንዋጋበት፣ ከእግዚአብሔር ጋር ያለንን ቅርበትና ቤተሰባዊነት የምናሻሽልበት፣ ምሥጢራችንን ለአምላካችን የምንናገርበት፣ ድሆችን የምናስብበት ጊዜ ነው፡፡ ስለዚህም የሚጾም ሁሉ በሥጋ ፈቃዱ ላይ ድል ይቀዳጃል፣ የለመነውን ያገኛል፣ ሰማያዊ የሆነውን ምሥጢር ለማየት ከዓላማዊ ነገሮች ተለይቶ ይነጠቃል፣ በዓለም እየኖረ ከዓለሙ ይለያል፡፡ ዮሐ.15÷19፡፡
ተጨማሪ ያንብቡ
|
|
እግዚአብሔር አምላክ ሰውን የስሙ ቀዳሽ የርስቱ ወራሽ ይሆን ዘንድ ከምድር አፈር አበጅቶ የሕይወት እስትንፋስ እፍ ብሎበት በአርአያውና በአምሳሉ በዕለተ ዓርብ ፈጠረው። ዘፍ 1፥26-28። በፀጋ የከበረ ሆኖ ፈጣሪውን እያገለገለ የተፈጠረበትን ዓላማ ለ7 ዓመት በመጠበቅ እግዚአብሔርን ደስ እያሰኘ በክብር ኖረ። ዘፍ2፥7። ዳሩ ግን በሰባተኛው ዓመት በሰይጣን ምክር አማካኝነት የተሰጠውን ሕግ አፍርሶ ዕፀ በለስን በላ፤ በዚህም ምክንያት ከክብሩ ተዋርዶ ከገነት ተባሮ በምድረ ፋይድ ተጣለ። ዘፍ 2፥16-17 ሞተ ሥጋ ሞተ ነፍስ ተፈረደበት። ዘፍ 3፥ 1-17። ባህርይው ጐሰቆለ፤ አዳምና ሔዋን የዲያብሎስ አገልጋይ ሆኑ። በእንዲህ ያለ ጽኑ ፍርድ ውስጥ እያሉ አዳም ስለበደሉ አዘነ፤ አለቀሰ፤ ፈጣሪውንም ይቅርታ ጠየቀ። የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔርም በፈጠረው ፍጥረት ሳይጨክን ”ከአምስት ቀን ተኩል በኋላ ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንሃለሁ“ የሚል የምሕረት ተስፋ ሰጠው። አዳምም ተስፋውን እየጠበቀ አምስት ሺህ አምስት መቶ ዘመን ያህል ምህረትን ሲናፍቅ ኖረ። ዘፍ 3፥16። 
ተጨማሪ ያንብቡ
|
|
|