View in English alphabet 
 | Monday, September 06, 2010 ..:: ማኅበረ ቅዱሳን ::.. Register  Login
if ye have word of exhortation for the people, say on

 በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ በሰ/ት/ቤ/ማ/መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን በሰሜን አሜሪካ ማዕከል የተዘጋጀውና ሚያዝያ 11 እና 12/ 2ዐዐዐ ዓ.ም (April 19 - 20, 2008) ለ2 ቀናት በዳላስ ከተማ (Richardson civic center) ለዕይታ የበቃው ዐውደ ርእይ በተሳካ ሁኔታ ተጠናቀቀ፡፡ 

ስለ ዝግጅቱ በዳላስ ከተማ ሬዲዮ የቀረበውን ዘገባ ያዳምጡ  

 

  ተጨማሪ ያንብቡ



ማኅበረ ቅዱሳን በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ በእግዚአብሔር ፈቃድ የተጀመረ የኦርቶዶክሳውያን ወጣቶች መንፈሳዊ እንቅስቃሴ የወለደው ነው፡፡ ለዚህ መንፈሳዊ እንቅስቃሴ መጀመር ቁጥራቸው ከአምስት የማይበልጡ ኦርቶዶክሳውያን ተማሪዎች ምክንያት ከመሆናቸው በቀር በወቅቱ ዛሬ የምናውቀውን ማኅበረ ቅዱሳን ለመመሥረት በሰው የተነደፈ ዓላማና ለዚያ ሲባልም የተሠራ አንድም ተግባር አልነበረም፡፡ ይሁን እንጂ ይህን መንፈሳዊ እንቅስቃሴ ለመጀመር ምክንያት የሆኑ ሁኔታዎች መኖራቸው ግልጥ ነው፡፡ እነዚህም ከዚህ በመቀጠል የሚጠቀሱት ናቸው፡
  ተጨማሪ ያንብቡ



የሰንበት ት/ቤቶች አንድነትና የአንድነት ፍሬ በተለያዩ አጋጣሚዎች ታይቷል፡፡ይሁን እንጂ አንድነቱ የተጠናከረ ባለመሆኑ የተከሰቱ ችግሮችም አሉ፡፡ ለአንድነቱ መላላት ምክንያት የሆኑቱን በሁለት ከፍሎ መመልከት መልካም ነው ፡፡እነርሱም ዉጫዊና ዉስጣዊ ችግሮች ናችዉ፡፡

ዉጫዊ ቸግሮች 

  • መናፍቃን በሰንበት ት/ቤቶች መካከል በሚነዙት አሉባልታ የሚፈጠረዉ መራራቅ
  • የሰንበት ት/ቤቶችን ዓላማ ባለመረዳትና በምግባረ ብልሹ ተማሪዎች የተነሳ የሚፈጠረዉ የተሳሳተ አመለካከት
  • የሚመለከታቸዉ አንዳንድ የቤተ ክርስቲያን ክፍሎች በየአህጉረ ስብከቱ ለሰንበት ት/ቤቶች መጠናከር የሚያደርጉት ድጋፍ አነስተኛ መሆን 
  ተጨማሪ ያንብቡ



Copyright 2007 by Mahibere Kidusan USA Center  | Terms Of Use | Privacy Statement