|
ነገረ ቅዱሳን
ከመልአከ ሰላም ደጀኔ ሺፈራው
«አልብኪ ነውር ወኢምንትኒ ላዕሌኪ፤» መኃ 4:7
የትንቢተ ነቢያት ማረፊያ ፡-የስብከተ ሐዋርያት መነሻ.የሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ምሥጢር ነገረ ማርያም ነው፡፡ ያለ ነገረ ማርያም ነገረ ክርስቶስን መናገር አይቻልም፡፡ በክርስትና ሃይማኖት ታሪክ የተነሡ አያሌ መናፍቃን የመጀመሪያ ችግራቸው የነገረ ማርያምን አማናዊ ትምህርት መቀበል ነበር ፡፡ ያም ችግራቸው ክርስቶስን በትክክል እንዳያምኑት አድርጓቸዋል፡፡ በነገረ ማርያም ላይ የተጣራ ትምህርትና እምነት ቢኖራቸው ኖሮ ለኑፋቄ አይጋለጡም ነበር ፡፡ ንስጥሮስ፡- «አምላክ ወልደ አምላክ» ብሎ በክርስቶስ ለማመን የተሳነው « ወላዲተ አምላክ . ወላዲተ ቃል. እመ እግዚአብሔር » ብሎ በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም ለማመን በመቸገሩ ነበር፡፡ PDF
ተጨማሪ ያንብቡ
|
|
ነገረ ቅዱሳን
«ብዙኀን ማርያም» እየተሰኘ በየዓመቱ መስከረም ሃያ አንድ ቀን በድምቀት የሚከበረው ይህ በዓል ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን («ወልድ») «ፍጡር» ነው (ሎቱ ስብሐት) ብሎ ያስተማረው የክህደት አስተማሪ የተወገዘበት፣ ሰይጣን ያፈረበት፣ ራሱን በበትረ መስቀል የተቀጠቀጠበት በዓል ነው፡፡
ተጨማሪ ያንብቡ
|
|
ኅብረ ነገር
“ ወገብረ ሰላመ በዲበ መስቀሉ”
በመስቀሉ ሰላምን አደረገ
በቀሲስ ስንታየሁ ደምሴ
መስቀል የሚለው ቃል የተገኘው “ሰቀለ” ከሚለው የግእዝ ቋንቋ ግሥ ነው፡፡ትርጓሜውም “የተመሳቀለ” ወይም “መስቀል” ማለት ነው፡፡
መስቀል ለክርስቲያኖች የሕይወትና የድኅነት ምልክት የሆነው መድኅን ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ ከተሰቀለበት ጊዜ ጀምሮ ነው፡፡
በኦሪት መስቀል የመርገምና የመቀጫ መሣሪያ ሆኖ ይቆጠር ነበር፡፡ ”ማንም ሰው ለሞት የሚያበቃውን ኃጢአት ቢሠራ እንዲሞትም ቢፈረድበት በእንጨትም ላይ ብትሰቅለው በእንጨት ላይ የተሰቀለ በእግዚአብሔር ዘንድ የተረገመ ነውና ሬሳው በእንጨት ላይ አይደር” ዘዳ 21:22-23
የጥንት ሮማውያን ወንጀለኞችን በመስቀል ተሰቅለው እንዲሞቱ ማድረግ ልማዳቸው ነበር፡፡ክርስቶስ ኢየሱስ ለድኅነተ ዓለም ከመሰቀሉ በፊት የእርግማን ምልክት የነበረው የመስቀል ታሪክ ጌታችን ከተሰቀለበት በኃላ ግን ታሪኩ ተቀይሯል፡፡PDF
ተጨማሪ ያንብቡ
|
|
የዲሲ እና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አብርሃም አዲስ ዓመትን ምክንያት በማድረግ ቃለ ምዕዳን እና ቡራኬ አስተላለፉ፡፡
 |
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ፩ አምላክ አሜን፡፡
በአለንበት አገር በሰሜን አሜሪካ፤ በሀገራችን በኢትዮጵያና በልዩ ልዩ አኅጉራት የምትገኙ አባቶቼና እናቶቼ ወንድሞቼና እኅቶቼ …
ተጨማሪ
|
|
|
ይህ ስለ ማኀበረ ቅዱሳን ማንነትና አገልግሎት የሚያስተነትነው ሦስተኛ ሣምንት ልዩ መርሐ ግብራችን ነው። በዚህ ዝግጅታችን ሁለት የማኀበሩ አባላትን እናቀርብላችኋለን። እንግዶቻችን በማኀበሩ ውስጥ ለረዥም ጊዜ በተለያዩ የአገልግሎት ሥፍራዎች ያገለገሉት መምህር ብርሃኑ ጎበና እና ዲያቆን ኤፍሬም እሸቴ ይሆናሉ።
ባለፉት ሁለት እሑዶች (8/23/2009 እና 8/30/2009) በተላለፉ የሀገር ፍቅር ሬዲዮ ዝግጅቶች አባ ኃ/ሚካኤል ወልደ ተ/ሃይማኖት የተባሉ ግለሰብ የማኀበረ ቅዱሳንን መልካም አገልግሎትና ስም የሚያጠቁር ቃለ ምልልስ ማድረጋቸውና እኛም ለዚያ መልስ የሚሆን አንድ ዝግጅት ማቅረባችን ይታወሳል። ግለሰቡ በዋነኝነት ያነሷቸውን ተጨማሪ ነጥቦች መነሻ በማድረግ ይህንን ቀጣይ ዝግጅት እናቀርባለን። እንደ መልካም የቤተ ክርስቲያን አገልጋይና ኦርቶዶክሳዊ አባት በመምሰል፣ ሳይላኩ እንደተላኩ፣ ሥልጣን ሳይኖራቸው እንደባለ ሥልጣን፣ ከተመደቡበት ሥፍራ ጠፍተው መጥተው ሳለ ልክ ተሹመው እንደመጡ በማሰመሰል በውጪ ሀገር (በዳያስጶራ) ያለውን ምእመን ለማሳሳት በመሞከር ላይ ያሉትን የእኒህን ሰው ማንነትና ግብር በምንመለከትበት በዚህ ዝግጅት የተለያዩ ጥያቄዎችን ለእንግዶቻችን በማቅረብ በጥልቀት እንወያያለን።
መልካም ጊዜ።
|
|
|