View in English alphabet 
 | Monday, September 06, 2010 ..:: መቅድም ::.. Register  Login
if ye have word of exhortation for the people, say on
አማርኛ




ላክ   ተወው
ስብከተ ወንጌል

(በቀሲስ ስንታየሁ አባተ)
በኢሳይያስ ዘመን የነበሩ እስራኤላውያን የተናገሩት ቃል ነው:: እስራኤላውያን የሚጾሟቸው ብዙ አጽዋማት ነበሯቸው:: ለምሳሌ ያህልም ብናይ በሳምንት ሁለት ጊዜ በሳምንት ሁለት ቀን ይጾሙ እንደነበር በሉቃስ ወንጌል ምዕ. 18¸12 ላይ ያለው ቃል ያስረዳል:: ማክሰኞና ሐሙስ ሊቀ ነቢያት ሙሴ ወደ ደብረ ሲና የወጣበትንና ከዚያ የወረደበትን ዕለት ለማሰብ እስራኤላውያን በሳምንት ሁለት ቀኖች ይጾሙ ነበR:: በነቢዩ በዘካርያስ ትንቢትም ላይ እግዚአብሔር እስራኤላውያንን እንዲህ ብሎ አዝዟቸዋል::"የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔር ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል የአራተኛው ወር ጾም የአምስተኛውም የሰባተኛውም የአስረኛውም ወር ጾም ለይሁዳ ቤት ደስታና ተድላ የሀሴትም በዓላት ይሆናል ስለዚህም እውነትንና ሰላምን ወደዱ" ተብሎ ለእስራኤላውያን ከእግዚአብሔር ዘንድ በነቢዩ በኩል በተነገራቸው መሠረት የተጠቀሱትን ይጾሙ ነበረ:: ዘካ. 8 18ና19

  ተጨማሪ ያንብቡ



የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ሕማምና መከራ ከመወለዱ በፊት አንስቶ እንዳልተለየው መጽሐፍት ያስረዳል፡፡ ከእነዚህ ሕማማትና መከራ እጅግ አብዝቶ የተቀበለው ቤዛነት በሚፈጽምበት በመጨረሻ ወቅት ነበር፡፡ አዳም የፈጠረውንና የሚወደውን አምላኩን በመበደሉና ትዕዛዙን በመጣሱ ከእግዚአብሔር ተጣልቶና ተለይቶ ይኖር ነበር፡፡ በዚህም የተነሳ ሕማም መከራ ውድቀትና ውርደት ደረሰበት፡፡ በሰውና በእግዚአብሔር ትልቅ የጥል ግድግዳ ተፈጠረ፡፡ እግዚአብሔር አምላክ ርኅሩኀ ስለሆነ የአዳም ስቃይ ስላሳዘነው ሊታረቀው አንድያ ልጁን ወደ ዓለም ላከው፡፡ እርሱም ሁለተኛው አዳም በመባል ክርስቶስ ኃጢአት በሌለበት ሰውነቱ የመጀመሪያው ሰው የአዳምን ኃጢአት ተሸክሞ የእርሱን ሞት ሞቶ በመስቀል ላይ የሕይወት መሰዋዕትነት በመክፈል ከራሱ፣ ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ አስታርቆታል፡፡ ይህንንም ነቢየ ልዑል ኢሣይያስ በትንቢቱ ከሰባት መቶ ዓመት በፊት እንዲህ ብሎ ገልጾት ነበር፡፡

  ተጨማሪ ያንብቡ



በዚህ በዐቢይ ርእሳችን የተመለከትነውን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ኃይለ ቃል የተናገረው ጌታችን መድኃነታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ የጸሎትና የጾምን ኃይልና ጥንካሬ አጉልቶ የተናገረውም ድዳና ደንቆሮ መንፈስ አድሮበት ይሰቃይ የነበረውን ብላቴና ከፈወሰ በኋላና የጌታ ተማሪዎች ርኩሱን መንፈስ ማውጣት እንዳቃታቸው ጥያቄ ከጠየቁ በኋላ ነበር፡፡ ተማሪ መምህሩን መጠየቅ የተለመደ እውነታ ነው፡፡ ልጁ ታሞበት ዕለት ዕለት ይሰቃይ የነበረው ግለሰቡ እርሱም ሆነ ልጁ ከገቡበት የመከራ አዘቅት ይወጡ ዘንድ ያስፈልገዋልና ከልጁ አጋንንቱን ያወጡ ዘንድ ወደ ደቀመዛሙርቱ አመጣው፡፡ ይሁን እንጂ ለመፈወስ አልተቻላቸውም፡፡ ከዚህ በኋላ ነበር የችግሮች ሁሉ ቁልፍ የሆነው የነገሥታት ንጉሥ፣የጌቴች ጌታ፣የታላቆች ታላቅ፣ኢየሱስ ክርስቶስን አይቶ በልጁ ላይ የሚታዩትን ችግሮች በሙሉ በግልፅ የነገረው፡፡

  ተጨማሪ ያንብቡ


ትምህርተ ሃይማኖት

በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ባሕልና ትውፊት መሠረት ይህ የያዝነው የጾም ወራት ከሰባቱ አጽዋማት አንዱና ዋነኛው፣ ጌታ ከተጠመቀ በኋላ የጾመው የአርባ ቀን ጾም ነው፡፡ ምእመናን ጌታቸው ያደረገውን ምሳሌ ተከትለው ይጾሙታል፡፡

  ተጨማሪ ያንብቡ


ትምህርተ ሃይማኖት

የጾም ወቅት መንፈሳዊ ተጋድሎዎች የሚበዙበት፣ ለእግዚአብሔር ያለንን ፍቅር የምንገልጥበት፣ እምነታችን የሚጠነክርበት፣ ከዲያብሎስ ጋራ የምንዋጋበት፣ ከእግዚአብሔር ጋር ያለንን ቅርበትና ቤተሰባዊነት የምናሻሽልበት፣ ምሥጢራችንን ለአምላካችን የምንናገርበት፣ ድሆችን የምናስብበት ጊዜ ነው፡፡ ስለዚህም የሚጾም ሁሉ በሥጋ ፈቃዱ ላይ ድል ይቀዳጃል፣ የለመነውን ያገኛል፣ ሰማያዊ የሆነውን ምሥጢር ለማየት ከዓላማዊ ነገሮች ተለይቶ ይነጠቃል፣ በዓለም እየኖረ ከዓለሙ ይለያል፡፡ ዮሐ.15÷19፡፡
  ተጨማሪ ያንብቡ


Page 6 of 24First   Previous   1  2  3  4  5  [6]  7  8  9  10  Next   Last   

 ፌስ ቡክ


  
 ገዳማትን ይርዱ Minimize

 

Help Monastries


  
 ግጻዌ


  
Copyright 2007 by Mahibere Kidusan USA Center  | Terms Of Use | Privacy Statement