|
ዘጌ የጣናን ሐይቅ ከምዕራብ ወደ ምስራቅ በመግፋት ተንሰራፍቶ የሚታይ ባሕር-ገብ መሬት ሲሆን በቅርብ ርቀት ሆነው ሲመለከቱት ክንፉን ዘርግቶ የተቀመጠ አሞራ ይመስላል፡፡ ዘጌ ከባሕር ዳር 15 ኪሎ ሜትር ያህል የሚርቅና በጀልባ ጉዞ አንድ ሰዓት ተኩል ያህል የሚወስድ ነው፡፡ በመኪና ለሚጓዝ ደግሞ ሁለት ሰዓት የሚወስድ 23 ኪሎ ሜትር ያህል የሚርቅ ነው፡፡
ተጨማሪ ያንብቡ
|
|
ዜና
በጣና ሐይቅ ዙሪያ ከሚገኙት የዘጌ ገዳማት መካከል አንዱ የሆነው የመሐል ዘጌ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን የካቲት 5 ቀን 2002 ዓ.ም ከቀኑ 12፡00 ሰዓት ጀምሮ የአደጋዉ ምክንያት ባልታወቀ እሳት ሙሉ በሙሉ ወድሟል። እሳቱን ለማጥፋት በገዳሙ ዙሪያ የሚገኙ ምዕመናን፣ በአካባቢው የሚገኘው የኢትዮጵያ መከላከያ ኃይል እና ከባሕር ዳር ከተማ በጀልባ ተሳፍረው የሄዱ ምዕመናን ጥረት ቢያደርጉም የእሳቱን ቃጠሎ ለመከላከል እና ለማጥፋት ሳይቻላቸው ቀርቷል።
ተጨማሪ ያንብቡ
|
|
ዜና
(በሻምበል ጥላሁን):
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የነገረ መለኮት ምሩቃን ማኅበር ከአሶሳ ሀገረ ስብከት ጋር በመተባበር ባደረገው ሐዋርያዊ ጉዞ ከአራት ሺሕ በላይ ሰዎች የክርስትና ጥምቀት እንዲጠመቁ ማስቻሉን አስታወቀ፡፡ "የነገረ መለኮት ምሩቃን ማኅበር" ለስምዐ ጽድቅ ጋዜጣ ዝግጅት ክፍል በላከው መረጃ እንዳስታወቀው፤ ሐዋርያዊ ጉዞና ጥምቀቱ የተከናወነው ከታኅሣሥ 16 እስከ 25 ቀን 2002 ዓ. ም የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሄኖክ፣ ሥራ አስኪያጁ ሊቀ መዘምራን ሐረገወይን ጫኔ፣ የከማሽ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ሥራ አስኪያጅ መልአከሰላም ተገኝ ጋሻው በተገኙበት ነው፡፡
ተጨማሪ ያንብቡ
|
|
ዜና
(በደረጀ ትዕዛዙ)
በማኅበረ ቅዱሳን የሕንፃ ግንባታ ጽ/ቤት አሳታሚነት ለኅትመት የበቃው «እመ ምኔት» የተሰኘው የደራሲ ፀሐይ መላኩ አዲስ ረጅም ልብወለድ መጽሐፍ ተመረቀ፡፡ ጥር 9 ቀን 2002 ዓ.ም አንጋፋና ወጣት ደራሲያን፣ የሃይማኖት አባቶች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በሩስያ ባህል ማዕከል /ፑሽኪን አዳራሽ/ የተመረቀው መጽሐፍ፤ በገዳማውያን ሕይወትና በውስብስብ ወንጀል ታሪክ ላይ ያተኮረ ሲሆን ደራሲዋ የመጽሐፉን ሸያጭ ገቢ ለማኅበሩ ጽ/ቤት ሕንፃ ግንባታ እንዲውል አበርክተዋል፡፡ የማኅበረ ቅዱሳን ምክትል ዋና ጸሐፊ እና የሕንፃ አሠሪ ኮሚቴው ተወካይ ዲያቆን ዋስይሁን በላይ በዚሁ ምረቃ ወቅት ባስተላለፉት መልእክት፤ ማኅበረ ቅዱሳን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ሥር ሆኖ ለበርካታ ዓመታት መንፈሳዊና ማኅበራዊ አገልግሎት ሲያበረክት መቆየቱን ጠቅሰው ይህንኑ አገልግሎት በተጠናከረ ሁኔታ ለማከናወን የጽ/ቤት ሕንፃ ግንባታ እያካሄደ ነው ብለዋል፡፡
ተጨማሪ ያንብቡ
|
|
ትምህርተ ሃይማኖት
(በመሐር ቸሬ አበበ)
በፍትሐ ነገሥት መንፈሳዊ አንቀጽ 15 እንደተገለጸው ቅዱሳን አባቶቻችን ሥጋ ለነባቢት ነፍስ እንድትታዘዝና የፈቲው ፆርም እንዲደክም የሚያደርግ የሰውን ልጅ ከእግዚአብሔር ጋር እንዲገናኝ የለመነውም ልመና መልስ እንዲኖረው እጅግም የሰይጣንን ፍላጻ ወይም ጦር ለመስበር የሚያስችል ኃይል ያለው መሣሪያ ጾም ነው፡፡ ነቢየ እግዚአብሔር «በእግዚአብሔር አምላካችን ፊት ራሳችንን ዝቅ እናድርግ፣ በእርሱም ዘንድ ጾምን አወጅኩኝ። ስለዚህ ነገር ጾምን፣ ወደ እግዚአብሔርም ለመንን እርሱም ተለመነን፡፡» እንዳለ የሰው ልጅ የነፍሱን ነገር በማሰብ በጾም እግዚአብሔርን ሊለምን ሊማጸን የሚፈልገውን ሁሉ ሊጠይቅ ይገባል፡፡ ከነቢዩ ዕዝራ የምንማረው በጾም ለሕዝብና ለራስ ለምኖ ዋጋ ማግኘትን ነው፡፡
ተጨማሪ ያንብቡ
|
|
|