|
ከመልአከ ሰላም ደጀኔ ሺፈራው ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ድኅነተ ዓለምን በመስቀል ላይ ከፈጸመ በኋላ በአካለ ሥጋ ወደ መቃብር ወረደ ÷ ይኸውም በመቃብር ፈርሶ በስብሶ መቅረትን ሊያስቀር ነው፡፡ በአካለ ነፍስ ደግሞ ወደ ሲኦል ወረደ ÷ ይኸውም በሲኦል ለነበሩ ነፍሳት ነፃነትን ይሰብክላቸው ዘንድ ነው፡፡ መለኮት በተዋሕዶ ከሥጋም ከነፍስም ጋር ነበረ፡፡ ለዚህ ነው መቃብር ሥጋን ሊያስቀረው ያልቻለው ፡፡ ሲኦልም ነፍስን ማስቀረት አልተቻለውም ፡፡ ቅዱስ ዳዊት ፡- « ነፍሴን በሲኦል አትተዋትምና ቅዱስህንም መበስበስን ያይ ዘንድ አትተዋትምና ፤ » ያለው ይኽንን ታላቅ ምሥጢር በትንቢት ቃል ሲናገር ነው ፡፡ መዝ 15 ÷ 10 ፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስም ፡- « ክርስቶስ ደግሞ ወደ እግዚአብሔር (ወደ አብ ÷ ወደ ራሱና ወደ መንፈስ ቅዱስ) እንዲያቀርበን እርሱ ጻድቅ ሆኖ ስለ ዓመፀኞች አንድ ጊዜ በኃጢአት ምክንያት ( ስለ ሰው ልጆች ኃጢአት ተላልፎ በመስጠት) ሞቶአልና ፤ በሥጋ ሞተ (በፈቃዱ ነፍሱን ከሥጋው ለየ) ÷ በመንፈስ ግን ሕያው ሆነ ÷ (ያን ሥጋ ነፍስ እንድተለየችው መለኰት አልተለየውም) ÷ በእርሱም ደግሞ (መለኰት በተዋሐዳት ነፍስ) ሄዶ በወኅኒ ለነበሩት ነፍሳት ሰበከላቸው፤
ተጨማሪ ያንብቡ
|
|
Share
በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ በሰ/ት/ቤ/ማ/መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን በአሜሪካ ማዕከል አዘጋጅነት በላስ ቬጋስ ለሁለት ቀናት ክፍት ሆኖ የቆየው ‹‹የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን፡- ትናንት - ዛሬ - ነገ›› ዐውደ ርእይ በደመቀ ሁኔታ ተካሄደ፡፡
ተጨማሪ ያንብቡ
|
|
ኅብረ ነገር
በዐቢይ ጾም ውስጥ ካሉት ሳምንታት መካከል አራተኛው እሑድ መጻጉዕ ይባላል፡፡ መጻጉዕ የተባለበት ምክንያት በዚሁ ሰንበት ከዋዜማው ጀምሮ የሚዘመረው ጾመ ድጓ ድውያንን መፈወሱን ዕራንን ማብራቱን የሚያነሣ በመሆኑ ነው፡፡ «38 ዓመት የታመመውን መጻጉዕን ኢየሱስ አዳነው» እንዲሁም ልጁ የታመመበት የመቶ አለቃው «ጌታዬ በቃልህ እዘዝ ልጄ ይድናል፡፡ በቤቴ ጣርያ ሥር አንተ ልትገባ አይገባህም» አለው:: «ጌታ በሚያልፍበት መንገድ አንድ ዕውር ፈውሰኝ» ብሎ ጮኸ የሚመሩት ሰዎች ዝም በል አሉት፡፡ ዕውሩ ግን እምቢ ብሎ «የዳዊት ልጅ ጌታ ይቅር በለኝ ዕርዳኝ» እያለ ጩኸቱን ቀጠለ፡፡
ተጨማሪ ያንብቡ
|
|
ኅብረ ነገር
ከዐቢይ ጾም ሳምንታት ሦስተኛው ሰንበት ምኩራብ ተብሎ የተሰየመበት ምክንያት በዚሁ ዕለት የሚዘመረው ጾመ ድጓ ከዋዜማው ጀምሮ እስከ ሰላሙ ድረስ በዕለተ ሰንበት «ቦአ ኢየሱስ ምኩራበ አይሁድ»
«ኢየሱስ በሰንበት ቀን ወደ አይሁድ ምኩራብ ገባ» እያለ ኢየሱስ በአይሁድ ምኩራብ ማስተማሩን እየጠቃቀሰና እያነሣሣ ስለሚዘምር ይህን ሰንበት ለዚህ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በምኩራብ እየገባ ለማስተማሩና በምኩራብ የሚሸጡ የሚለውጡ ነጋዴዎችን ለማስወጣቱ ቤተ መቅደሱን ለማስከበሩ መታሰቢያ ሆኖ ስለተሰጠ ነው፡፡ የዚህም በዓል ታሪክ ዝርዝር ሁኔታው በማቴዎስ ወንጌል ምዕ 21፡12-13 ተጠቅሷል፡፡
ተጨማሪ ያንብቡ
|
|
- “’በስተኋላዬ ያለውን እየረሳሁ በፊቴ ያለውን ለመያዝ እገሰግሳለሁ’ የሚለውን የቅዱስ ጳውሎስን ቃል ልናስታውስ ይገባናል” (ብፁዕ አቡነ በርናባስ የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ)
- “የፈረሰውን ቤተ ክርስቲያን ለመስራት ሁላችንም እንረባረብ” (ክቡር አቶ አያሌው ጎበዜ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ርእሰ መስተዳደር)
የመሐል ዘጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን የተተከለው በ1292ዓ.ም. ሲሆን በርካታ ጥንታውያን ስዕላት፣የብራና መጻሕፍትና ሌሎች ቅርሶች የሚገኙበት ቤተ ክርስቲያን ነው። ቤተ ክርስቲያኑ ከ1986-1989ዓ.ም. እድሳት ተደርጎለት ከ1989 ጀምሮ ሙሉ አገልግሎት ሲሰጥ ቆይቷል። ቤተ ክርስቲያኑን ሙሉ በሙሉ ያወደመው እሳት ባልታወቀ ምክንያት የተነሣው የካቲት 5 ቀን 2002 ዓ.ም. ከቀኑ 11፡00 ሰዓት አካባቢ ነበር። እሳቱ ከተነሣበት ጊዜ ጀምሮም የገዳሙ ማኅበረሰብና የአካባቢው ምእመናን እሳቱን ለማጥፋት ከፍተኛ ጥረት አድርገዋል። የእሳቱ መነሣት በክልሉ መንግስት እንደተሰማም የመከላከያ ሠራዊት ፣የፖሊስ እና የአየር ኃይል አባላት በክልሉ መንግስት ትዕዛዝ ወደ ቦታው ሔደው እሳቱን የማጥፋትና እሳቱ እንዳይዛመት ጫካውን የመመንጠር እንዲሁም የጥበቃ አገልግሎት ሲሰጡ አድረዋል። የእሳት አደጋ መኪናዎች ወደ አካባቢው ቢሄዱም በመንገዱ አስቸጋሪነት ምክንያት ከዘጌ ከተማ ሊያልፉ አልቻሉም።
ተጨማሪ ያንብቡ
|
|
|