View in English alphabet 
 | Monday, September 06, 2010 ..:: መቅድም ::.. Register  Login
if ye have word of exhortation for the people, say on
አማርኛ




ላክ   ተወው
ስብከተ ወንጌል

የጌታችን ትንሳኤ በአበው ዘንድ በምሳሌ የተመሰለ፣ በነቢያት በትንቢትና በምልክት የተነገረ፣ በተስፋ የተጠበቀ የድኅነታችን ታላቅ በር ነው፡፡ የጌታችንን የወንጌል ምሥራች የሰበኩ ሐዋርያትም የጌታን ትንሳኤ በደስታና በጽናት መስበካቸው ትንሳኤው በኃጢአትና በሞት ላይ የተደረገ ታላቅ ድልና የድኅነት የምሥራች በመሆኑ ነው፡፡ ስለዚህም የትንሳኤው ምስክሮች ሆነዋል፡፡ /የሐ.ሥራ 2፡32/ ጌታ የተነሳበት ሰንበተ ክርስቲያንም የበዓላት በኩር፣ የዘላለም ሕይወት ቀብድ፣ ዘላለማዊት መባሏ የጌታ ትንሳኤ የምዕመናን የዘላለም ሕይወት ትንሳኤ በኩር በመሆኑ ነው፡፡ /1ኛቆሮ. 15፡20/

  ተጨማሪ ያንብቡ


ስብከተ ወንጌል

(ዲ/ን ዮሐንስ ልሳነወርቅ)
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ማታ ማታ እየወጣ የሚያድርባት፣ሐሙስ ሌሊት በይሁዳ በኩል ለአይሁድ ተላልፎ የተሰጠባት፣ሐዋርያት ስለ ነገረ ምጽአት ጠይቀው የተረዱባት፣ከሙታን ተለይቶ በተነሣ በአርባኛው ቀን ጌታችን ያረገባት ተራራ -ደብረ ዘይት። ዐርገ የሚለው የግዕዝ ግስ ዐረገ፣ወጣ በሚሉት የአማርኛ ቃላት የሚፈታ ሲሆን ዕርገት የሚለው ስምም ማረግን፣ መውጣትን፣አወጣጥን ያመለክታል።(አ.ኪ.ክ መ.ቃ)

አስቀድሞ ክቡር ዳዊት እንደተናገረው መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደቀመዛሙርቱ እያዩት ወደ ሰማይ ዐርጓል። ዐርገ እግዚአብሔር በይባቤ፤ወእግዚእነ በቃለ ቀርን - እንዲል መዝ. 46፥5። ጌታችን በእውነት እንዳረገ ይኽም ሊታመን የማይችል እንዳልሆነ የቤተ ክርስቲያን ሊቅ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ያስረዳል። ሕማም የሚስማማው ግዙፍ ሥጋን ተዋሕዶ ሳለ ከስቅለቱ አስቀድሞ በባሕር ላይ ከሄደ፡ ዛሬ ነፋስን ከፍሎ ሲያርግ ቢታይ ማንም ማን አይጠራጠር፤ሥጋው አልተለወጠምና። ሃይ.አበው ዘዮሐ.አፈ.ክፍል 13 ቁጥር 15

  ተጨማሪ ያንብቡ


ትምህርተ ሃይማኖት

ቤተ ክርስቲያናችን ለምን ስለ እመቤታችን ዘወትር እንደምታስተምር አንዳንድ ሰዎች ግር ሲላቸው ይታያል:: እንዲያውም “አላዋቂ ሳሚ …” እንዲሉ ስለ እመቤታችን ማስተመሯ ስለ ጌታችን እንዳታስተምር አድርጓታል ብለው የሚናገሩ አሉ:: ቤተ ክርስቲያናችን ግን ስለ አመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የምታስተምረው ለርሷ ካላት ስለጌታችን የምታስተምረው አልቆባት አይደለም:: ምክንያቱም ከኢትዮጵያ ሊቃውንት በላይ ለነገረ መለኮት ምሑርና ጥንቁቅ ከማግኘት የሰማይን ስፋት ልክ ማግኘቱ ሳይቀል አይቀርም:: 

  ተጨማሪ ያንብቡ


ኅብረ ነገር

ብፁዕ አቡነ አብርሃም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሰሜን አሜሪካ የሰሜን ምሥራቅና ምዕራብ አሜሪካ የኒውዮርክ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የጌታችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን



      እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው በሰላም አደረሰን

ብፁዕ አቡነ አብርሃም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የዲሲ እና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የጌታችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን  የትንሣኤ በዓል ምክንያት በማድረግ ያስተላለፉት ቃለ ምዕዳን እና ቡራኬ 

 

  


Page 3 of 24First   Previous   1  2  [3]  4  5  6  7  8  9  10  Next   Last   

 ፌስ ቡክ


  
 ገዳማትን ይርዱ Minimize

 

Help Monastries


  
 ግጻዌ


  
Copyright 2007 by Mahibere Kidusan USA Center  | Terms Of Use | Privacy Statement