View in English alphabet 
 | Thursday, May 23, 2013 ..:: መቅድም ::.. Register  Login
if ye have word of exhortation for the people, say on
አማርኛ




ላክ   ተወው
ምስጢራተ ቤተ ክርስቲያን

 ሐዋርያዊትና ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሰዎች የእግዚአብሔርን ልጆች ይሆኑ ዘንድ በሥላሴ ስም ታጠምቃለች፡፡ ይህም ጌታ ራሱ ለሐዋርያቱ ‹‹ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም  ያጠመቃችኋቸው፡፡››  (ማቴ. 28÷19) ብሎ የሰጠውን አምላካዊ ቃል መሠረት በማድረግ ነው፡፡ ስለዚህ ቤተክርስቲያን በክርስቶስ ደም ከተመሠረተችበት ዘመን አንስቶ በሥላሴ (በአብ፣ በወልድ፣ በመንፈስ ቅዱስ) ስም መጠመቅ የድኀነት በር ቁልፍ መሆኑን ስታስተምርና ተግባራዊ ስታደርግም ኖራለች፡፡
  ተጨማሪ ያንብቡ


ምስጢራተ ቤተ ክርስቲያን

ጥምቀት የማትደገም፣ የማትከለስ አንዲት ናት፡፡ብርሃነ ዓለም ቅዱስ ጳውሎስ ልጅነትን የምናገኝባት ጥምቀት የማትደገምና የማትከለስ አንዲት ብቻ መሆንዋን ሲያስተምር ‹‹አንድ ጌታ አንድ ሃይማኖት አንዲት ጥምቀት…አለ›› ብሏል (ኤፌ.4÷5)፡፡ ሃይማኖታቸው የቀና 318ቱ ሊቃውንትም ‹‹ኃጢአትን በምታስተሠርይ በአንዲት ጥምቀት እናምናለን፡፡››

  ተጨማሪ ያንብቡ


ኅብረ ነገር

በቅርቡ ተደርጎ የነበረው የ1999 ዓ.ምሕረቱ የሕዝብ ቆጠራ ከቤተ ክርስቲያናችን አንጻር ስላለው ምንነት የተዘጋጀውን የፍኖተ ሰላም ሬዲዮ ዝግጅት ያዳምጡ።

የሕዝብ ቆጠራው የልዩ ዝግጅታችን አካል የሆነበት ዋነኛው ምክንያት ቆጠራውና ውጤቱ በጉጉት ሲጠበቅ ስለነበርና በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን በኩልም የሚኖረው ትርጉም ሰፊ ስለሚሆን ነው።

በጠቅላላው በቆጠራውና በተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ከዲያቆን ኤፍሬም እሸቴ ጋር ቆይታ አድርገናል እንድትከታተሉ እንጋብዛለን።  አስተያየት ወይም ጥያቄ ካለዎት በአድራሻችን ይላኩልን።    



ኅብረ ነገር

ምክሮች - 1
• የሕይወት መገኛ የሆነውን አምላክህን እወቅ፡፡ በእርሱም ታመን፡፡ እርሱንም ተስፋ አምባና መጠጊያ በማድረግ ኑር፡፡
• ሕይወት ውጣ ውረድ የሚበዛባት ደስታና ሐዘን የሚፈራረቅባት መድረክ በመሆኗ ሁኔታዎችን እንዳመጣጣቸው በትእግሥትና በማስተዋል ለማሳለፍ ተጣጣር፡፡
• በሕይወት ዘመንህ በምታፈራው ገንዘብ የተራበን በማብላት የተጠማን በማጠጣት የታረዘን በማልበስና ችግረኞችን በመርዳት ጽድቅንና መልካም ስምን አትርፍበት፡፡
• ሕይወት በብቸኝነት እጅግ መራራ ናትና በጊዜ ከአምላክህ ጋር ተነጋግረህ የኑሮ ጓደኛህን በመምረጥ በመፈቃቀር በመተሳሰብና በመተጋገዝ ለመኖር ተዘጋጅ፡፡

  ተጨማሪ ያንብቡ


ዜና

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተሕዋዶ ቤተክርስቲያን ሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን የአውሮፓ ማዕከል ልሳነ ተዋሕዶ የተሰኘ መንፈሳዊ የፓልቶክ አገልግሎት ጀመረ።

ማዕከሉ የአዲሱን የፓልቶክ አገልግሎት የሙከራ ስርጭት ከኅዳር ፲፭ እስከ ፳፱ ቀን ፳፻፩ ዓ.ም. ሲያደርግ  ቆይቶ ታኅሳስ ፩ ቀን ፳፻፩ ዓ.ም. ምሽት ለሦስት ሰዓታት በቆየ  የመክፈቻ ሥነ ስርዓት መደበኛ ስርጭቱን በይፋ ጀምሯል

  ተጨማሪ ያንብቡ


Page 29 of 34First   Previous   24  25  26  27  28  [29]  30  31  32  33  Next   Last   

 የሬድዮ እና ቴሌቪዥን አገልግሎት Minimize

ስብከተ ወንጌልን በሬድዮ እና ቴሌቪዥን የማጠናከር አገልግሎት እናግዝ

ማኅበረ ቅዱሳን የሬድዮ አገልግሎት በዚህ ዓመት መጀመሩ የታወቃል። እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ለረጅም ጊዜ ሲጠበቅ የነበረው የቴሌቪዥን አገልግሎት በየሳምንቱ እሑድ ከ5፡30 እስከ 6፡00 ሰዓት የሚቆይ ተጀምሯል። በኢንተርኔት ላይ http://eotc.tv ድረ ገጽ ላይ መከታተል ይችላሉ። አገልግሎቱን ሁላችንም በጸሎት እንድናስብ እና ለምዕመናን በምንችለው ሁሉ በማድረስ ለአገልግሉቱ ስፋት የበኩላችንን እንድናደርግ በእግዚአብሔር ስም ለማሳሰብ እንወዳለን።

አገልግሎቱን በገንዘብ ለመደገፍ ይህን ገጽ መጠቀም ይችላሉ።


  
 ገዳማትን ይርዱ Minimize

 

Help Monastries


  
 ሶሻል ኔትወርኪንግ

Share |

  
 ግጻዌ


  
Copyright 2007 by Mahibere Kidusan USA Center  | Terms Of Use | Privacy Statement