|
ይህ ስለ ማኀበረ ቅዱሳን ማንነትና አገልግሎት የሚያስተነትነው ሁለተኛ ሣምንት ልዩ መርሐ ግብራችን ነው። በዚህ ዝግጅታችን ሦስት የማኀበሩ አባላትን እናቀርብላችኋለን። እንግዶቻችን በማኀበሩ ውስጥ ለረዥም ጊዜ በተለያዩ የአገልግሎት ሥፍራዎች ያገለገሉት መምህር ብርሃኑ ጎበና፣ ቀሲስ ያሬድ ገብረ መድኀን እና ዲያቆን ኤፍሬም እሸቴ ይሆናሉ።
ባለፈው እሑድ (8/23/2009 በተላለፈ የሀገር ፍቅር ሬዲዮ ዝግጅት አባ ኃ/ሚካኤል ወልደ ተ/ሃይማኖት የተባሉ ግለሰብ የማኀበረ ቅዱሳንን መልካም አገልግሎትና ስም የሚያጠቁር ቃለ ምልልስ አድርገዋል። ግለሰቡ በዋነኝነት ያነሷቸውን ነጥቦች መነሻ በማድረግ ይህንን ዝግጅት እናቀርባለን። እግዚአብሔር ለማህበሩ የሰጠውን የአገልግሎት ጸጋና የፈተና ጽናት በምንመለከትበት በዚህ ዝግጅት የተለያዩ ጥያቄዎችን ለእንግዶቻችን በማቅረብ በጥልቀት እንወያያለን። መልካም ጊዜ። ሬዲዮ ዝግጅታችንን ያድምጡ
የማኀበረ ቅዱሳን መተዳደሪያ ደንብ
|
|
ሌሊቱ አልፎ መዓልቱ ሲተካ ጨልሞ የበረው ሲገለጥ፣ ወጋገን ሲታይ ‹ነጋ፣ ጠባ› ይባላል፡፡ የመስከረምም መጥባት እንደዚሁ ነው፡፡ መስከረም ሲጠባ፣ ጠቁሮ ጨልሞ የነበረው ሰማይ ይገለጣል፡፡ የውኃ ሙላቱ ይጐድላል፡፡ ደፍርሶ የነበረው ይጠራል፡፡ ምድር በልምላሜ ታጌጣለች፡፡ በአበቦች ታሸበርቃለች፡፡ ሁሉም ነገር የዘመኑን መለወጥ ለማብሠር ብሩህ ይሆናል፤ ይደምቃል፡፡
ተጨማሪ ያንብቡ
|
|
ማኀበረ ቅዱሳን በጠቅላይ ቤተ ክህነት ሥር ካሉት መምሪያዎች አንዱ በሆነው የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ሥር አገልግሎት የሚሰጥ መሆኑ ይታወቃል። ሕገ ደንቡና መመሪያውም የጸደቀለት በቅዱስ ሲኖዶስ ነው። የሚሰጠው አገልግሎት በሙሉ በየደረጃው በሚገኙ የቤተ ክርስቲያኒቱ አካላት የሚታወቅ ሲሆን በየዓመቱም ስለዚሁ አገልግሎቱ ሪፖርት ያቀርባል። በገንዘብ ደረጃም ማኀበሩ የሚጠቀምበት የገቢ ምንጭ ከገቢያቸው አንድ በመቶ ወይም 1% ከሚያዋጡት አባላቱ የሚገኝ ሲሆን ይህንንም የሚያስቀምጠው ጠቅላይ ቤተ ክህነት በደብዳቤ በሚከፍትለት ሕጋዊ የባንክ መዝገብ ነው።ሬዲዮ ዝግጅታችንን ያድምጡ
ተጨማሪ ያንብቡ
|
|
ነገረ ቅዱሳን
ቤተ ክርስቲያናችን ለምን ስለ እመቤታችን ዘወትር እንደምታስተምር አንዳንድ ሰዎች ግር ሲላቸው ይታያል፡፡ እንዲያውም ‹‹አላዋቂ ሳሚ...›› እንዲሉ ስለ እመቤታችን ማስተማå ስለ ጌታችን እንዳታስተምር አድርጓታል ብለው የሚናገሩም አሉ፡፡ ቤተ ክርስቲያናችን ግን ስለ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የምታስተምረው ለርሷ ካላት ልዩ ፍቅር ብቻ ወይም ስለጌታችን የምታስተምረው ለርሷ ካላት ልዩ ፍቅር ብቻ ወይም ስለጌታችን የምታስተምረው አልቆባት አይደለም፡፡ ምክንያቱም ከኢትዮጵያ ሊቃውንት በላይ ለነገረ መለኰት ምሁርና ጥንቁቅ ከማግኘት የሰማይን ስፋት ልክ ማግኘቱ ሳይቀል አይቀርም፡፡
ተጨማሪ ያንብቡ
|
|
ዛሬ ነሐሴ 9/2001 ዓ.ም (August 15/2009) የተላለፈውን የ“ፍኖተ ሰላም” ሬዲዮ ዝግጅታችንን ያድምጡ ። አስተያየቶቻችሁን በሚከተለው አድራሻ ማድረስ ትችላላችሁ።
Cellphone: (1) 240-899-5215
Mahibere Kidusan Office: office@mahiberekidusan.org
MAHIBERE KIDUSAN North America Sub Center Office
P.O. Box 13041
Silver Spring, MD 20911 USA
ተጨማሪ ያንብቡ
|
|
|