View in English alphabet 
 | Monday, September 06, 2010 ..:: ፕሮጀክቶች ::.. Register  Login
if ye have word of exhortation for the people, say on


ገዳማትና አድባራት፤የአብነት(የቆሎ) ት/ቤቶችንና ሊቃውንት መምህራኑን በመርዳት የሺህ ዓመታት ታሪክ ይጠበቃል፡፡ በታሪክ ፊት መልካም ስም የሚያተርፈውን ይህንን በጎ አገልግሎት ይራዱ፡፡ በአበው ጸሎት ይጠበቃሉ ፤ በእግዚአብሔር በረከት እርስዎና ቤተሰብዎ ይትረፈረፋሉ፡፡   

  የአብነት መምህራንና ተማሪዎች ቀጥተኛ ድጎማ ከመስከረም እስከ ነሐሴ 2001 ዓ.ም የሚያስፈልግ የበጀት ዝርዝር ከተለዩ በጎ አድራጊዎች ገንዘብ ገቢ እንዲሆን የሚጠበቅ

  ተጨማሪ ያንብቡ



መካነ ሰማዕት ቅዱስ ገላውዴዎስ ቤተ ክርስቲያን በደቡብ ጎንደር ሀገረ ስብከት በደራ ወዳ በገላውዴዎስ ቀበሌ የሚገኝ ሲሆን ቤተ ክርስቲያኑን ያሠሩት አፄ ገላውዴዎስ ናቸው፡፡ወቅቱ በግራኝ አህመድ ወረራ ብዙ አብያተ ክርስቲያናት የተቃጠሉበት ብዙ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን የተሰውበት ወቅት ነበር፡፡ ይህ ወረራ በሸዋ በትግራይ ጦርነት ከፍቶ ስለነበር አንድ ባህታዊ ወደ ንጉሡ ቀርበው በስውር ሁለት ታቦታት አሉና እነዚህን ታቦታት ይዘው ካልሄዱ ድል አያደርጉም ብለው በንጉሡ ስለነገሯቸው የእመቤታችንንና የሰማዕቱ የቅዱስ ገላውዴዎስን ታቦታት ካህናትን አስይዘው ወደ ጦርነቱ ሲሄዱ አሁን ቤተ ክርስቲያኑ ባለበት ቦታ አቅራቢያ ሲደርሱ ካህኑ የነበሩባት በቅሎ አልሄድ ትላለች፡፡ በዚህ ጊዜ እግዚአብሔር የሚያደርገው አይታወቅምና ድል አድርጌ ብመለስ የሰማዕቱ የቅዱስ ገላውዴዎስን ቤተ ክርስቲያን አሠርቼ ሲሶ መንግሥት ሰጥቼ አነግሠዋለሁ ብለወ ቃል ሲገቡ ታቦታቱ ተንቀሳቅሰው ወደ ጦርነት እንደሄዱ ይነገራል፡፡

  ተጨማሪ ያንብቡ



ገዳሙ በደቡብ ምዕራብ በጅማ ሃገረ ስብከት በዳቡና ቀበሌ ገበሬ ማኀበር ከአዲስ አበባ 345 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ይገኛል፡፡በጥንት ጊዜ አብርሃ አጽብሐ ዘመን ጀምሮ ክርስትና በአካባቢው መስፋፋት ጀምሮ በኋላም በኢትዮጵያ መካከለኛው ዘመን /The Medival Period of Ethiopia/ ጊዜ ከምንም በላይ ክርስትና ተስፋፍቶ የነበረበት ወቅት ነበር፡፡ ከዚያ በኋላ ግን በግራኝ አህመድ ወረራ ዘመቻና በዘመነ መሳፍንት በነበረው የእርስ በእርስ ጦርነት ምክንያት ደቡብና ምዕራብ ክፍል ከሰሜኑ ያገኝ የነበረውን ካህናት ማግኘት ባለመቻሉ ትልቅ ክፍተት ተፈጥሮ ነበር፡፡

  ተጨማሪ ያንብቡ



የመካነ ሕይወት አቡነ ተክለ ሃይማኖት ገዳም በባሌ ሀገረ ስብከት ከአዲስ አበባ 445 ኪ.ሜ / ከጎባ የ45 ደቂቃ የእግር መንገድ/ በኋላ ወጣ ብሎ በደን በተሸፈነ ኮረብታማ ቦታ ላይ ይገኛል፡፡ገዳሙ በውል አይታወቅ እንጂ እንደ ሌሎቹ ገዳማት በአሥራዎቹ ዓመታት ወስጥ እንደነበር በቦታው የሚገኙ መረጃዎች ይመሰክራሉ፡፡ በገዳሙ በጥንታውያን ዋሻዎች ውስጥ የሚገኙ ጽላቶች እና የቀደምት አበው አጽሞች ተገኝተዋል፡፡ ገዳሙ እንደገና የመሠረተወ ኀዳር 3ዐ ቀን 1977 ዓ.ም ሲሆን ከተመሠተ በኋላ ለረጅም ጊዜያት የቅዳሴ፤ የኪዳን፤ የሰዓታትና የማኀሌት አልግሎት በተሟላ ሁኔታ ይከናወን ነበር ለማለት ያስቸግራል፡:

  ተጨማሪ ያንብቡ


Page 1 of 2First   Previous   [1]  2  Next   Last   

Copyright 2007 by Mahibere Kidusan USA Center  | Terms Of Use | Privacy Statement