በብፁእ አቡነ ፊሊጶስ የጠቅላይ ቤተ ከህነት ስራ አስኪያጅ እና የኢሊባቡርና የጋምቤላ ሊቀ ጳጳስ ለማተሚያ ቤቶች እና ለቤተ ክህነት የተለያዩ መምሪያዎች በግልባጭ በተላከ ደብዳቤ በሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ሃላፊ በአባ ሠረቅ ብርሃን ወልደ ሳሙኤል ለማተሚያ ቤቶች የተላከው የእግድ ደብዳቤ ተነሳ::
ይህን በመጫን ሙሉ ደብዳቤውን ይመልከቱ።
(አትላንታ፤ ጆርጂያ)፦ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰንበት ት/ቤቶች ማ/መምሪያ ሥር መንፈሳዊ እና ማሕበራዊ አገልግሎቶችን የሚሰጠው የማ/ቅዱሳን የአሜሪካ ማዕከል 13ኛ ጠቅላላ ዓመታዊ ጉባኤውን በአትላንታ/ ጆርጂያ በመካሔድ ላይ ነው። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የዲሲ እና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የሆኑት ብፁዕ አቡነ አብርሃም፣ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን እና በአሜሪካ ግዛቶች ውስጥ የሚገኙ አባላት በተገኙበት በመካሔድ ላይ ያለው ይህ ጉባኤ በቅዳሜ ከሰዓት በፊት ግንቦት 20/2003 ዓ.ም ውሎው የማዕከሉን የ2003 ዓ.ም ዓመታዊ የተግባር ድርጊቶች ሪፖርት ከማዳመጡም በላይ በቀረቡት ሪፖርቶች ላይ ውይይት አድርጓል።